እኛ የቀድሞው የኢትዮጵያ አትሌትች በ1990 ዎቹ ኢትዮጵያ ሀገራችንን ወክለን አለም አቀፍ ውድድሮችን በማድረግ የሀገራችንን ሰንደቃላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ኢትዮጵያ የሀገራችንን ስም እያስጠራን የቆዩን ስንሆን አሁን ደግሞ የአትሌቲክስ ውድድርን ካቆምን በሗላ በእንግሊዝ ሀገር ኑሮአችንን መስርተን ስንኖር በተለያዩ አጋጣሚዎች የኢትዮጵያዊያንን ኮሚኒቲ ለበርካታ አመታት በገንዘብ ሆነ በሃሳብ ነፃ ግልጋሎት ስንሰጥ ቆይተናል:: አሁን ደግሞ በዚህ ባለንበት ሀገር በአትሌቲክስ ሙያችን ያለንን የሩጫ እውቀትና ያካበትነውን ልምድ ለሌላው ህብረትሰብ ለማካፈልና በእንግሊዝ ሀገር የሚገኙትን የኢትዮጵያን ኮሚኒቲዎች ሁሉ በስፖርት ለማሰባሰብ የሩጫ ውድድሮችን በማዘጋጀትንይ በማሳተፍ የመገናኘት ባህሉን አዳብሮ ለመጪው ትውልድ ጥሩ ተምሳሌት ሆኖ እንዲተላለፍ በአመት ሁለት ሦስት (2-3) ግዜ የውድድር ዝግጅት ለማዘጋጀት እየሰራን እንገኛለን:: ስለዚህ ማንኛውም ኮሚኒቲ ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ከጎናችን ሆናችሁ ለምታደርግሉን የገንዘብም ሆነ የሀሳብ ድጋፍ ከወዲሁ እያመሰገንን ኑና አብረን እንሩጥ እንላለን::
1, ማህበረሰቡ የእስፖርት ፍላጎት እንዲኖረውና እለት ከእለት እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ማበረታታት
2, የሩጫ ውድድሮችን በማዘጋጀት ኮሚኒቲው አድስ ባህል እንዲያዳብር ማድረግ
3, በእሩጫ ውድድ አሸናፊ የሚሆኑትን ወጣቶች ለተሻለ ውጤት እንዲበቁ ክትትልና በማበረታታት ድጋፍ ማድረግ
4, በአትሌቲክስ ጥሩ ተሳትፎ ያላቸውን ወጣቶች ክለብ ተመዝግበው ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ምክርና አቅጣጫ መስጠት
5, አስፈላጊ ሆኖ ገተገኘ የስልጠናና የምክር አገልግሎት መስጠት
6, የኢትዮጵያ አትሌቶች በአለም ላይ ውድድር ሲያደርጉ ውጤታቸውን ተከታትለን በመገናኛ መረባችን ለማህበረሰቡ ማሳዎቅ
7, በአጠቃላይ ማህበረሰባችን የእስፖርት ግንዛቤና ጥቅሙን እንዲያቅና ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው::
ዝግጅቶች (activity)
• አድዋ ድል 5ኪ ሜ
• ታላቁ እሩጫ በለንዶን 10ኪ ሜ
• ኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ዝግጅት ትብብር
• የተለያዩ የኮሚኒቲ ዝግጅቶችን ማዘጋጀት
About former Ethiopian Athlets
We, the former Ethiopian athletes, represented our country in international competitions during the 1990s, and made our country’s flag fly high. We raised the profile of our nation, and now that we have retired from professional athletics, we have established our lives in the UK. For many years, we have been providing free services to the Ethiopian community, both financially and intellectually.
Currently, we are working to share our knowledge and experience in running with other members of the community, and to bring together all Ethiopian communities in the UK. We aim to achieve this by organizing running competitions. Therefore, we would like to thank all community organizations and individuals for their financial and emotional support, and invite everyone to join us.
Our objectives are as follows:
1. To encourage the community to take an interest in sports and engage in daily physical activities.
2. To create a new culture of Athletics racing within the community through organized events.
3. To support and encourage young people who win races to achieve even better results.
4. To provide guidance to young people to develop their athletic skills and register in the club.
5. To offer necessary training and counseling services.
6. To follow the progress of Ethiopian athletes in international competitions and share results with the community.
7. To promote the benefits of sports and encourage the society to take up sports.
Our activities include:
• Adwa victory 5km
• The Great Ethiopian Run in London 10km
• Ethiopian sports and culture federation festival
• Organizing various community events.
Copyright © ETHIO ATHELETS All Rights Reserved.