Adwa Victory l5km 2024

298Views

ሰላም ለምንወዳችሁና  ለምናከብራችሁ  ዉድ የስፖርት  ቤተሰቦች  በሙሉ  በቅድሚያ  የከበረ  ሰላምታችን  እያቀረብን፦

የዘንድሮውን   የአድዋ  የድል  ቀን  የ5km የሩጫ  ውድድር  በ26/05/2024 እንደምናዘጋጅ  ቀደም  ብለን  ማሳወቃችን  ይታወቃል  በተጨማሪ  ደግሞ  ከዉድድሩ የሚገኘው ገቢ ከወጪ  ቀሪው  በሙሉ  በሀገራችን ኢትዮጵያ  በችግር  ላይ  ላሉ እናቶችና ህፃናት  እንዲሁም  ከፍተኛ  ችግር  ለገጠማቸው  የቀድሞው የኢትዮጵያ  አትሌቶች  እንዲስጥ  አዘጋጅ  ቡድኑ ወስኗል

የሚገኘውን  ትርፍ  ገንዘብ ለወገኖቻችን   እንዲሰጥ  ከወሰን   ወጪን  ለመቀነስ ደግሞ ግድ  ይላል   ስለዚህ  ትልቁ  ወጪያችን  ደግሞ ዉድድሩ የሚዘጋጅበት ቦታ (ፓርክ) ነው::  ባለፈው  ዓመት  ታላቁ  ሩጫ  የተደረገበት  ፓርክ  ብዙ  ወጪ  ስለሚያስወጣን መመዝገቢያውን  £25 ለአዋቂዎች እንዲሁም  ለወጣቶች  ከ18  አመት በታች   £17  ለማድረግ አስበናል  ሌላው  ደግሞ  ሌላ  ፓርክ  እንዲዘጋጅ  ካደረግን  የመመዝገቢያውን ዋጋ  £20 ለአዋቂዎች  £15  ለወጣቶች ይሆኖል ማለት ነው።  ለዚህ  ውሳኔ  እናተም  እንድትሳተፉ  ስለፈለግን  ምርጫችሁን  እንድታስታውቁን  ባክብሮት  እንጠይቃለን::

1,   Battersea Park. ይሁን እና  £25  ቢከፈል አይጎዳንም ለምትሉ 1  ቁጥርን ብቻ ማስቀመጥ፤ 

2,   ብሮክዎል ፖርክ ወይም ሌላ ፓርክ  ይሁንልን  እና  £20  እንክፈል  ለምትሉ  2 ቁጥርን ብቻ በማስቀመጥ ፈጣን መልሳችሁን እንዲሰጡን  በአክብሮ ለማሳሰብ  እንወዳለን ::

መልካም  ቀን እንመኛለን  

የቀድሞው  የኢትዮጵያን  አትሌቶች  ማህብር በዩኬ

Leave a Reply